በቴሌግራም፣ በቲክቶክና በፌስቡክ ለሚሸጡ

ደንበኞችዎ መደወል ሳያስፈልጋቸው ከቴሌግራም ሱቅዎ የሚፈልጉትን ያዛሉ

አንድ ጊዜ ሊንክዎን ለደንበኞችዎ ያጋራሉ። ደንበኞችዎ የሚፈልጉትን ምርት መርጠው ትዕዛዛቸውን ይልካሉ፤ ክፍያውም በቀጥታ ወደ ቴሌብር ወይም የባንክ ሂሳብዎ ይገባል።

ለ30 ቀናት በነፃ ይጠቀሙ፤ ምዝገባውም ሙሉ በሙሉ ነፃ ነው።

የሙከራ ትዕዛዞችን በሥራ ሰዓት እኛ በቀጥታ እናስተናግዳለን።

አዲስ ትዕዛዝETB 3,400 · ማድረስ
የቴሌግራም ሱቅ፦ ዕቃዎች ከነፎቶአቸውና ከነዋጋቸው
የትዕዛዞች ዝርዝር፦ ዋጋና የትዕዛዝ ደረጃ
ተከፍሏልደረሰኙ ከትዕዛዙ ጋር ተያይዟል
ገንዘቡ በቀጥታ ወደ እርስዎ
ቴሌብር ወይም ማንኛውም ባንክ
ለደንበኞች መተግበሪያ አያስፈልግም
30 ቀን በነፃ

አሁንም "ለማዘዝ ይደውሉልን" እያሉ ነው?

ዛሬ

  • ስልክ ሳያነሱ ሲቀሩ፣ ደንበኛዎ ወደ ሌላ ሻጭ ሊሄድ ይችላል።
  • የሚሸጡትን ዕቃዎች ፎቶ እያነሱ አንድ በአንድ ለደንበኞች ይልካሉ።
  • የክፍያ ደረሰኞችን ከብዙ መልዕክቶች መካከል መፈለግ ያስቸግራል።
  • "ትዕዛዜ ከምን ደረሰ?" ብለው ደንበኞች ደጋግመው ይደውላሉ።

በTCOS

  • ሱቅዎ ሁልጊዜ ክፍት ነው፤ ደንበኞችዎም በፈለጉት ሰዓት ያዛሉ።
  • ሁሉንም ዕቃዎችዎን በአንድ ቦታ፣ ከነዋጋቸው ጋር በአንድ ሊንክ።
  • ደረሰኞች ከትዕዛዞቻቸው ጋር ተያይዘው አንድ ላይ ይቀመጣሉ።
  • ደንበኞችዎ የትዕዛዛቸውን ሁኔታ በቀጥታ ማየት ይችላሉ።

ከሱቅ ሊንክ እስከ ክፍያ፦ TCOS እንዴት ይሰራል?

እውነተኛ የTCOS ገጾችን ከሙከራ ሱቃችን ይመልከቱ። የስልክ ቁጥሮች ለደህንነት ሲባል ተደብቀዋል።

  1. የቴሌግራም ሱቅ፦ ዕቃዎች ከነፎቶአቸውና ከነዋጋቸው1

    ደንበኛው የሱቅዎን ሊንክ ይከፍታል።

    ሱቅዎ በቴሌግራም ውስጥ ይከፈታል፤ ደንበኛውም ሁሉንም ዕቃዎች ከፎቶና ከዋጋው ጋር ያያል።

  2. በዳሽቦርድ ላይ ያለ የትዕዛዝ ጥያቄ፦ ዕቃዎች፣ ስም፣ ማድረሻ ወይም መውሰጃ፣ እና Create order2

    ትዕዛዙ ከሁሉም አስፈላጊ መረጃዎች ጋር ይደርስዎታል።

    የታዘዙ ዕቃዎች፣ የደንበኛ ስም፣ ስልክ ቁጥር እና የማድረሻ ወይም የመውሰጃ መረጃ።

  3. ከቦቱ የተላከ መልዕክት፦ ድምሩና የክፍያ መረጃው3

    ቦትዎ የክፍያ መረጃዎን ለደንበኛው ያሳያል።

    የሚከፈለው ጠቅላላ ድምርና የቴሌብር ወይም የባንክ ሂሳብዎ መረጃ።

  4. የMark as paid መስኮት፦ የክፍያ መንገድና የማሳያ ደረሰኝ4

    ደረሰኙን አይተው ክፍያውን ያረጋግጣሉ።

    ቦቱም ለደንበኛው የማረጋገጫ መልዕክት ይልካል።

  5. የደንበኛው ገጽ፦ ትዕዛዙ ያለበት ደረጃ5

    ደንበኛው ትዕዛዙ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ይከታተላል።

    እርስዎ ጋር ስልክ መደወል ሳያስፈልገው።

TCOSን ለምን ይመርጣሉ?

ገንዘቡ በቀጥታ እርስዎ ጋር ይደርሳል።

ደንበኛው ወደ ቴሌብር ወይም የባንክ ሂሳብዎ በቀጥታ ይከፍላል። ገንዘቡ በTCOS በኩል አያልፍም።

ቴሌብር ወይም ባንክ፣ በደረሰኝ ማረጋገጫ

የክፍያ መረጃዎ (ቴሌብር፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ አዋሽ… የሚፈልጉትን) ከቦትዎ ይላካል፤ ደንበኛው የደረሰኙን ፎቶ ይልካል፤ እርስዎ አይተው "ተከፍሏል" ይላሉ።

ሁሉም ትዕዛዞች በአንድ ቦታ!

ትዕዛዞችዎና መልዕክቶችዎ በአንድ ቦታ ያገኛሉ። "Needs action" ደግሞ ቀጣይ ትኩረት የሚፈልጉ ሥራዎችን ያሳይዎታል።

በአድራሻ ማድረስ ወይም ከሱቅ መውሰድ።

ትዕዛዙን ሲያረጋግጡ የማድረሻ ክፍያው ከድምሩ ጋር ይደመራል፤ ከፈለጉ ደንበኞች ከሱቅዎ መጥተው እንዲወስዱ ማድረግ ይችላሉ።

ያለቀ ዕቃ አይታዘዝም።

ብዛቱን ካስገቡ፣ 5 ወይም ከዚያ በታች ሲቀር ሱቁ ስንት እንደቀረ ለደንበኛው ያሳያል።

በስልክዎም ይጠቀሙበት!

ዳሽቦርዱን ከስልክዎ መጠቀም ይችላሉ፤ ማሳወቂያዎችንም ማብራት ይችላሉ።

በአራት ቀላል እርምጃዎች ይጀምሩ!

  1. ይመዝገቡ

    የንግድዎ ስም፣ ኢሜይልና የይለፍ ቃል ብቻ ያስፈልጋሉ። ምዝገባዎ እስኪፀድቅ ድረስ ምርቶችዎን ማስገባትና ቦትዎን ማዘጋጀት ይችላሉ። ምዝገባዎ ከፀደቀ በኋላ ደንበኞችዎ ትዕዛዝ መስጠት ይችላሉ።

  2. ቦትዎን ያገናኙ

    የራስዎን ነፃ የቴሌግራም ቦት ይፍጠሩ። እንዴት እንደሚፈጥሩት የሚያሳዩ ደረጃዎችን እዚህ ያገኛሉ።

  3. ምርቶችዎን ይጨምሩ

    ፎቶ፣ ዋጋ (በብር)፣ መጠንና ቀለም ያስገቡ።

  4. ሊንኩን ያጋሩ

    በቴሌግራም ቻናልዎ፣ በቲክቶክና በፌስቡክ ላይ ያጋሩ። ደንበኞችዎ ትዕዛዝ ይሰጣሉ፤ እርስዎም ያረጋግጣሉ።

የቴሌግራም ቦትዎን በቀላሉ ይፍጠሩ!

  1. ቴሌግራምን ከፍተው @BotFather ን ይፈልጉ።
  2. /newbot ብለው ይላኩ። የቦትዎን ስምና በ"bot" የሚያልቅ ዩዘርኔም ይምረጡ።
  3. BotFather የሚሰጥዎትን Token ይቅዱ። ለሌላ ሰው አያሳዩት።
  4. ወደ TCOS ዳሽቦርድዎ ይመለሱ። Telegram ገጹን ከፍተው Token ን ይለጥፉ። ከዚያ Connect bot የሚለውን ይጫኑ።

ቦት መፍጠር ነፃ ነው። እገዛ ከፈለጉ @tcos_support ላይ ያነጋግሩን። ልንረዳዎት ዝግጁ ነን።

ዋጋና ክፍያ

30 ቀን በነፃ

ነፃ የሙከራ ጊዜ፤ ከዚያ ወርሃዊ ክፍያ።

ስለ ዋጋው @tcos_support ላይ ይጠይቁን።

  1. ዛሬ፦ ይመዝገቡየንግድ ስም፣ ኢሜይልና የይለፍ ቃል ብቻ ያስፈልጋሉ። ለመመዝገብ ምንም ክፍያ አይጠየቅም።
  2. ምዝገባዎ ሲፀድቅ፦ 30 ቀን በነፃየነፃ ሙከራ ጊዜው የሚጀምረው ምዝገባዎ ከፀደቀ በኋላ ነው።
  3. ከዚያ፦ በየወሩ በቴሌብር ይክፈሉክፍያው የሚፈጸመው እርስዎ ሲከፍሉ ብቻ ነው፤ ከሂሳብዎ በራሱ አይቆረጥም።

ለምን ያምኑናል

  • ገንዘብዎ በቀጥታ ወደ እርስዎ ይገባል።ደንበኞችዎ በቀጥታ ወደ ቴሌብር ወይም የባንክ ሂሳብዎ ይከፍላሉ። TCOS ገንዘብዎን አይይዝም።
  • እያንዳንዱን ሱቅ እናፀድቃለን።አዲስ ሱቆችን ከጠዋቱ 3:00 እስከ ምሽቱ 3:00 (የኢትዮጵያ ሰዓት) እናፀድቃለን። ብዙውን ጊዜ ሂደቱ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ይጠናቀቃል።
  • ሌላ ሻጭ የደንበኞችዎን መረጃ አያይም።እያንዳንዱ ሻጭ የራሱን ደንበኞች ብቻ ያያል።
  • በቴሌግራም ድጋፍ እናገኝዎታለን።እገዛ ከፈለጉ @tcos_support ላይ መልዕክት ይላኩልን።

ተደጋግመው የሚጠየቁ ጥያቄዎች

ዋጋው ስንት ነው?

የ30 ቀን ነፃ የሙከራ ጊዜ አለ። ከዚያ በኋላ በየወሩ በቴሌብር ክፍያ ይፈጽማሉ። ስለ ዋጋው @tcos_support ላይ ይጠይቁን።

ገንዘቡ ወዴት ይሄዳል? TCOS ገንዘቡን ይይዛል?

ደንበኛው በቀጥታ ወደ ቴሌብር ወይም የባንክ ሂሳብዎ ይከፍላል። TCOS ገንዘብዎን አይይዝም። የክፍያ ደረሰኙን አረጋግጠው ክፍያውን እንደተፈጸመ የሚያረጋግጡት እርስዎ ነዎት።

ደንበኞቼ መተግበሪያ ማውረድ አለባቸው?

አያስፈልግም። ቴሌግራም ብቻ በቂ ነው።

ደንበኞቼ በየትኛው ባንክ መክፈል ይችላሉ?

በመረጡት ባንክ መክፈል ይችላሉ። በክፍያ መረጃዎ ላይ የቴሌብር፣ CBE Birr ወይም የመረጡትን ባንክ ሂሳብ መረጃ ያስገባሉ።

የራሴ ቦት ያስፈልገኛል?

አዎ። BotFather በነፃ የራስዎን ቦት እንዲፈጥሩ ያስችልዎታል። የአፈጣጠሩ ደረጃዎች ከላይ ተብራርተዋል። እገዛ ከፈለጉም እንረዳዎታለን።

ደንበኛው ካልከፈለስ?

ትዕዛዙ በ"Payment pending" (ክፍያ በመጠባበቅ ላይ) ሁኔታ ይቆያል። ገንዘቡ ወደ ቴሌብር ወይም የባንክ ሂሳብዎ መግባቱን በደረሰኙ እስኪያረጋግጡ ድረስ ትዕዛዙን እንደተከፈለ ማስመዝገብ የለብዎትም። ትዕዛዙንም መሰረዝ ይችላሉ። በክምችት ብዛት የተመዘገቡ ዕቃዎች ካሉ፣ ትዕዛዙ ሲሰረዝ የዕቃው ብዛት ወደ ክምችቱ ይመለሳል።

ምርቶቼን ለደንበኞች ማድረስ እችላለሁ?

አዎ። ትዕዛዙን ሲያረጋግጡ የማድረሻ ክፍያው በጠቅላላ ዋጋው ላይ ይደመራል። ደንበኞችዎ ከሱቅዎ መጥተው ምርቶቻቸውን እንዲወስዱም ማድረግ ይችላሉ።

ስልኬ ብቻ በቂ ነው?

አዎ። ዳሽቦርዱን በስልክዎ መጠቀም ይችላሉ። እንደ መተግበሪያም በስልክዎ ላይ መጫንና ማሳወቂያዎችን ማብራት ይችላሉ።

ዳሽቦርዱ በአማርኛ ነው?

ዳሽቦርዱ ለጊዜው በእንግሊዝኛ ነው። የሱቅዎ ቁልፎችና የቦቱ ራስ-ሰር መልዕክቶችም በእንግሊዝኛ ናቸው። ነገር ግን የሱቅዎን ስም፣ የምርቶችዎን ስም፣ የክፍያ መረጃዎንና ለደንበኞችዎ የሚጽፏቸውን መልዕክቶች በፈለጉት ቋንቋ ማስገባት ይችላሉ።

የነፃ ሙከራ ጊዜው ካለቀ በኋላ ካልከፈልኩስ?

የነፃ ሙከራ ጊዜው ካለቀ በኋላ ለተጨማሪ 7 ቀናት መሸጥዎን መቀጠል ይችላሉ። ከዚያ በኋላ ክፍያዎ እስኪመዘገብ ድረስ አዲስ ትዕዛዞችን መፍጠርም ሆነ ማረጋገጥ አይችሉም። ቦቱና የሱቅዎ ገጽ ሱቁ ለጊዜው እንደማይገኝ ለደንበኞች ያሳውቃሉ። ከዚያ በፊት የተጀመሩ ትዕዛዞች ግን መስተናገዳቸውን ይቀጥላሉ።

ዛሬውኑ ይጀምሩ

ማሳያ ሱቁን እንደ ደንበኛ ይሞክሩት፣ ወይም የራስዎን ሱቅ በነፃ ይክፈቱ።

የሙከራ ትዕዛዞችን በሥራ ሰዓት እኛ በቀጥታ እናስተናግዳለን።